አቶ አቢይ ፋንታዬ ከአባታችው አቶ ፋንታዬ ደማ እና ከእናታቸው ወ/ሮ አረጋሸ ዋቦ በቀድሞዉ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ናዝሬት ከተማ ጥር 18 ቀን 1947 ዓ.ም ተወለዱ። እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርሱ በአጼ ገላውዲዎስ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ትምህርታቸዉን በማጠናቀቅ የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተናን ውስደው ጥሩ ዉጤት በማምጣት በቀድሞው የቀዳማዊ ሀይለስላሴ በአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገብተው ነበር።
በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ትምህርታቸውን ከመስከረም 2 ቀን 1965 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ወር ያህል ከተከታተሉ በኋላ የኢትዮጵያ የባሕር ሀይል ወጣቶችን በካዴትነት አሰልጥኖ በመኮንንነት እንደሚያስመርቅ ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት፣ ፍላጎት ስላደረባቸው የመግቢያ ፈተና ተፈትነው በማለፍ ወደ ምጽዋ ባሕር ሀይል ኮሌጅ ገብተዋል።
ከዚያም ምጽዋ ከነበረው የኢትዮጵያ ባሕር ሀይል ዋናው መደብ ትምህርታቸውን ለ4 አመት ተኩል በመከታተል በጥሩ ውጤት በመኮንንነት ማዕረግ ተመርቀዋል።
ከባሕር ሀይል ኮሌጅ ከተመረቁ በኋላ የባሕር ሀይል የምጽዋ መደብ ረዳት ፐርሶኔል በመሆን አገልግለዋል። ከዚያም አዲስ አበባ በሚገኘው የባሕር ሀይል ጠቅላይ መምሪያ ኤዲሲ (ADC) የባሕር ሀይል ዋና አዛዥ ጽ/ቤት ዋና ሀላፊ በመሆን ለ8 ወር ያህል ጽ/ቤቱን በሀላፊነት በመምራት ላይ ሳሉ በወቅቱ በነበረው የፖለቲካ አሰላለፍ የኢሕአፓ አባል ነህ በሚል ተጠርጥረው ለሁለት ዓመት ታስረው ተፈተዋል።
ከእሰር ከተፈቱም በዃላ ከ1972ዓ.ም ጀምሮ በባሕርና ትራንዚት አገልግሎት ኮርፖሬሽን በመቀጠር ከኦፊሰርነት እስክ መምሪያ ሀላፊነት ለ33 አመታት አገልገለው በጡረታ ተገልለዋል። በተጨማሪ በነበራቸው የትምህርት ፍላጎትና ራሳቸውን ይበልጥ ለማሻሻል በስራ ላይ እያሉ ትምህርታቸውን በመቀጠል በማኔጅመንት የመጀመሪያ ድግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተቀብለዋል።
በጡረታ ከተገለሉም ቡኹላ ለሶስት ዓመታት ያህል በግል ኩባንያ ተቀጥረው በትራንስፖርት መምሪያ ሃላፊነት አገልግለዋል።
ከየካቲት 2010 ዓ.ም ጀምሮ አሜሪካን አገር ካንሳስ ግዛት በመምጣት ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመልካም ሁኔታ በመኖር ላይ እያሉ ባደረባቸው ህመም ምክኒያት በህክምና ሲረዱ ከቆዩ በዃላ በተውለዱ በ 66 ዓመታቸው መጋቢት 25/2013 ዓ.ም ከዚህ ዓለም
በሞት ተለይተዋል።
አቶ አብይ ፋንታዬ ከወ/ሮ የሺሐረግ ታደስ ጋር መስከረም 25 ቀን 1973 ዓ.ም በህገ ጋብቻ በመተሳሰር ሁለት ወንዶችና አንድ ሴት ልጅ አፍርተው፣ አራት የልጅ ልጆችን አይተዋል ።
አቶ አብይ ፋንታዬ በሕይወት በነበሩበት ዘመን ደግ ሩህሩህና ቅን፣ በስራቸው ታታሪ እና ቅን አገልጋይ፣ ዘመድ ወዳድና ሰውን አክባሪ ትሁት ሰው ነበሩ።
ልዑል እግዜአብሔር ነፍሳቸውን በገነት ያሳርፍልን። ለቤተሰቦቻቸውና ለዘመዶቻቸው እንዲሁም ለወዳጆቻቸው ብርታትንና ጽናትን ይስጥልን።
Ato Abiy Fantaye Demma, 66, died Saturday, April 03, 2021 surrounded by his family. Born January 25, 1955, in Nazareth, Ethiopia, he was the son of Fantaye Demma and Aregash Wabo.
He graduated from Emperor Gelawdewos High School in 1972. Then he joined the College of Ethiopian Navy in 1977 and graduated after 4 and half years. He also graduated from Addis Ababa University and got his bachelor’s degree in management.
On October 05, 1980, he married Yeshihareg Tadesse in Nazareth, Ethiopia and had three children.
Ato Abiy was employed by the Ethiopian Maritime and Transit Service Corporation in 1979 and retired after working for 33 years. He enjoyed working night and day in his office. He spent most of his weekends with his family and friends. He also enjoyed reading books about history, politics, and old novels. He also spent his leisure time watching historical movies and documentaries. He devoted his time to his children and grandchildren whenever he could.
Ato Abiy is survived by his wife, one daughter, two sons, four grandchildren, two sisters, and one brother along with several nieces and nephews.
He was preceded in death by his parents, Fantaye Demma and Aregash Wabo.
SHARE OBITUARY
v.1.9.6